Search

ፒኤስጂ የሱፐር ካፕ አሸናፊ ሆነ

ሓሙስ ነሐሴ 08, 2017 186

ፒኤስጂ ቶተንሀም ሆትስፐርን በመለያ ምት በማሸነፍ የአውሮፓ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን አንስቷል፡፡
በጣልያን ብሉነርጂ ስቴዲየም በተደረገው የዋንጫ ጨዋታ ቶተንሀም ሆትስፐር እስከ 84ኛው ደቂቃ ድረስ ሚኪ ቫን ደቬን እና ክርስቲያን ሮሜሮ ባስቆጠሯቸው ግቦች 2 ለ 0 ሲመራ በሚቆይም ውጤቱን ማስጠበቅ አልቻለም፡፡
ፒኤስጂ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ተቀይረው የገቡት ሊ ካንግ ኢን እና ጎንካ ራሞስ ባስቆጠሯቸው ግቦች ጨዋታው ሁለት አቻ ተጠናቋል፡፡
አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው መለያ ምትም ፒኤስጂ 4 ለ 3 አሸንፏል፡፡
ማንችስተር ዩናይትድን በማሸነፍ ዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ያነሳው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አሳዛኝ ተሸናፊ ለመሆንም ተገዷል፡፡
የአለም ክለቦች ዋንጫን ለቼልሲ አሳልፎ የሰጠው ፒኤስጂ የአውሮፓ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫን የግሉ አድርጓል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ