የቼልሲ ተጫዋቾች ከዓለም ክለቦች ዋንጫ ካገኙት የገንዘብ ሽልማት ግማሹን በቅርቡ በመኪና አደጋ ሕይወታቸው ላለፈው ለዲየጎ ዦታ እና ወንድሙ አንድሬ ሲልቫ ቤተሰቦች ለመስጠጥ መወሰናቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል፡፡
በአሜሪካ በተደረገው የክለቦች ዓለም ዋንጫ የምእራብ ለንደኑ ክለብ ፒኤስጂን 3 ለ 0 አሸንፎ ዋንጫውን ባነሳበት ጨዋታ 114.6 ሚሊዮን ዶላር ማግኝቱም ይታወሳል፡፡
ከዚህ ውስጥ 15.5 ሚሊዮን ዶላር ለተጫዋቾች የሚከፋፈል ሲሆን እያንዳንዳቸው ከሚደርሳቸው ግማሹን ለፖርቹጋላዊው ኮከብ ቤተሰቦች እንደሚሰጡም ይፋ አድርገዋል፡፡
ዲየጎ ዦታ እና ወንድሙ አንድሬ ሲልቫ ከወር በፊት ባጋጠማቸው የመኪና አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ