Search

የአዲስ አበባን መለያ የተነቀሰችው ዝነኛ የሆሊውድ ተዋናይ

ሓሙስ ነሐሴ 08, 2017 156

እውቋ የሆሊውድ ተዋናይት እና በሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎቿ የምትታወቀው አንጀሊና ጆሊ የሰውነት ንቅሳቷ ከማጌጫነት ያለፈ ነው። 

አንጀሊና በሰውነቷ ላይ ንቅሳት ማድረግ የጀመረችው ከዓመታት በፊት ሲሆን፣ ወሳኝ የምትላቸውን ጉዳዮችን በንቅሳት መልክ በሰውነቷ ላይ ታሰፍራለች።

አንጀሊና ጆሊ ከተነቀሰቻቸው ምልክቶች መካከል በቀኝ ክንዷ ላይ  የከተሞች መለያ ኮድ ይገኛል ። ይህ  “N 9° 2' 0" E 38° 45' 0"  የሚለው ንቅሳት የዚህ ንቅሳት ትርጉም የጂፒኤስ መለያ ነው።

ይህም በጉዲፈቻ የወሰደቻት በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆነችውን አንደኛ ልጇን ዘሀራን ለማስታወስ ስትል የተነቀሰችው ነው። 

ቁጥሩ የአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ መለያ ኮድ ሲሆን፤ በሌላ አገላለጽ ይህንን ቁጥር ጉግል ላይ ብንፈልገው የአዲስ አበባን ካርታ ያሳያል። 

አንጀሊና ጆሊ በተጨማሪም  በትከሻዋ እና በክንዶቿ ላይ የተለያዩ ትርጉም ያላቸው ንቅሳቶችን አስፍራለች። 

ስለ እምነት እና የመንፈስ ብርታትን በተመለከተ የተጻፉ ጥቅሶች፣  የልጆቿን የልደት ቀን እና ስም እንዲሁም ከተለያዩ ሀገራት የወሰደቻቸው የጉዲፈቻ ልጆቿ የትውልድ ሀገር መለያ ኮድ ከንቅሳቶቿ መካከል ይገኙበታል።

በዚህም መሰረት ሜይ 13, 1940 የሚል የሮማውያን ቁጥር ያለበት ንቅሳትም ተነቅሳለች። 

ይህ ቀን የሚያመለክተው በ1950 ዎቹ የኢንግላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር  የነበሩት ዊንስተን ቸርችል እስካሁንም ዝነኛ የሆነውን  አባባል የተናገሩበት ቀን ነው።

ቸርችል በእለቱ ለሀገራቸው ሕዝብ ንግግር ባቀረቡበት ወቅት "ከደም፣ ከእንባ እና ከላብ ውጪ የምሰጣችሁ ነገር የለኝም" በማለት ተናገረው ነበር ። 

ይህ አባባላቸው እስካሁንም ድረስ የሚጠቀስ ሲሆን፤ አንጀሊና ጆሊም ይህንን ንግግር ለማሰብ ነው ቀኑን በግራ  ክንዷ ላይ የተነቀሰችው።

የአዲስ አበባን መለያ በሰውነቷ ላይ ተነቅሳ የምትዞረው ዝነኛ ተዋናይ አንጀሊና ጆሊ አዲስ አበባን ሰሞኑን የጎበኘች ሲሆን፤ ብሔራዊ ቤተመንግስት ተገኝታ ጉብኝት አድርጋለች ።

አንጀሊና ጆሊ በአዲስ አበባ በነበራት ቆይታ ከቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ጋር ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን ወደ ዓለም አቀፍ የጥበብ ኢንዱስትሪ ለመሳብ በምንችልባቸው ዘዴዎች ላይ ተወያይተዋል። 

በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተገኝታም የሆስፒታሉን የሥራ እንቅስቃሴ በመጎብኘት በግሎባል ሄልዝ ኮሚቴ (ጂኤችሲ) በኩል አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ ቃል መግባቷ ይታወሳል።


#EBC  #ebcdotstream  #AddisAbaba