Search

ሲዳማ ቡና ያሬድ ገመቹን አሰልጣኝ አድርጎ ለመሾም ተስማማ

ሓሙስ ነሐሴ 08, 2017 126

ሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ የቀድሞውን የወላይታ ድቻ አሰልጣኘ ያሬድ ገመቹን ለመሾም ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡

የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት እና የክለቡ የቦርድ አባል የሆኑት አቶ አምበሴ አበበ ከኢትቪ ስፖርት ጋር ባደረጉት ቆይታ አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ ሲዳማ ቡናን ለመረከብ መስማማታቸውን ገልፀዋል።

አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ ለሁለት አመታት በወላይታ ድቻ ቆይታ ካደረጉት በኋላ ቀደም ብለው በረዳት አሰልጣኝነት ወደ አገለገሉት ሲዳማ ቡና ለመመልስ መስማማታቸው ይፋ ሆኗል፡፡

አሰልጣኙ የሲዳማ ቡና ጊዜያዊ አሰልጣኝ የሆኑቱን አዲሴ ካሳን በመተካት 2 ዓመት ውል ለመረከብ ተስማምተዋል ተብሏል፡፡

አሰልጣኙ ክለቡን ከዚህ ቀደም ከነበረው ውጤት የተሻለ እንዲያስመዘግብ ለማድረግ እንደሚሰሩም ገልፀዋል።

አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ ከወላይታ ድቻ ባሻገር ሀድያ ሆሳናን ያሰለጠኑ ሲሆን በከፍተኛ ሊግ ደግሞ ደቡብ ፖሊስ እና ስልጤ ወራቤ የመሳሰሉት ክለቦችን ማሰልጠናቸው የሚታወስ ነው።

በሴራን ታደሰ