የኢትዮጵያውያን መገለጫ የሆነውን የአብሮነትና የወንድማማችነት እሴቶችን በማጎልበት ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር ለማስቻል እንተጋለን ሲሉ የጋምቤላ ክልል ወጣቶች ተናግረዋል፡፡
የጋምቤላ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወጣት ኛፔት ቶካት እና አማኑኤል ሳይመን ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ወጣቱ ትውልድ ከምንም በላይ ምክኒያታዊ በመሆንና ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት በሀገር ግንባታ ሂደት የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ወጣት መቅደስ ብርሃነመስቀል እና ሀና ገዛኸኝም እንደዚሁ የከተማው ነዋሪዎች ሲሆኑ፣ የሰላም ዋጋ በገንዘብ የማይተመን ስለመሆኑ አንስተዋል፡፡
አክለውም ሰላምን ለማስቀጠል ወጣቶች ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት እንዳለባቸውም ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ሰላምን በማፅናት ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲረጋጥ ለማስቻል፣ የተጀመረውን ጥረት ከግብ ለማድረስ የሁሉም ዜጋ ቅንጅታዊ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ነው ወጣቶቹ የገለፁት፡፡
በክልሉና በሀገሪቱ በሰላም ግንባታ የተገኙ ስኬቶችን ለማስረፅ የበኩላቸውን እንደሚወጡም የክልሉ ወጣቶች ተናግረዋል፡፡
በሚፍታህ አብዱልቃድር