ኒውካስል የፊት መስመር ተጫዋቹን ጃኮብ ራምሴን ከአስቶንቪላ ለማስፈረም ተስማምቷል።
ክለቡ ጃኮብ ራምሴን ከአስቶንቪላ በ40 ሚሊየን ፓውንድ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷልም ነው የተባለው።
ራምሴ ለጤና ምርመራ በቀጣይ ቀናት ወደ ኒውካስል ከተማ ይጓዛልም ተብሎ ይጠበቃል።
የ24 ዓመቱ ተጫዋች በሌሎች ክለቦች ቢፈለግም ኒውካስልን ተመራጭ መድረሻው አድርጎታል።
ተጫዋቹ ማሊክ ቲያውን ተከትሎ ወደ ኤዲ ሃው ቡድን ለመቀላቀልም ከጫፍ ደርሷል።
በቀጣይ ከአሌክሳንደር ኢሳክ ጋር ያለው ሁኔታ ከተስተካከለ፤ በኒውካስል በኩል በቅርቡ ተጨማሪ ፊርማዎች ይጠበቃሉ ሲል ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘግቧል።
በሴራን ታደሰ