Search

ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ ዓረቢያ ሁለንተናዊ ትብብርን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መከሩ

ረቡዕ ሐምሌ 01, 2018 81

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር አብዱላህ ቢን ሀሰን አል-ዛህራኒን ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይቱ ወቅት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያና በሳዑዲ ዓረቢያ መካከል ያለው የረጅም ዘመን የሁለትዮሽ ግንኙነትና ታሪካዊ ትስስር የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።

ሁለቱ ወገኖች በጋራ ፍላጎቶች እና በወቅታዊ ቀጣናዊ ሰላምና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ በስፋት የተወያዩ ሲሆን፤ በተለይም በተለያዩ የልማትና የኢኮኖሚ ዘርፎች ያለውን ሁለንተናዊ ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

በተጨማሪም ውይይቱ በአሁኑ ወቅት በሳዑዲ ዓረቢያ በሚገኙ የኢትዮጵያ ዜጎች ወቅታዊ ሁኔታና መብት ጥበቃ ዙሪያ ላይ ያተኮረ እንደነበር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።