Search

ኢቢሲ ተጠባቂውን የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በቀጥታ ለተመልካቾች ያደርሳል

ረቡዕ ሐምሌ 01, 2018 106

የ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዋንጫ ፍፃሜ ነገ በሲዳማ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መካከል በአዲስ አበባ ስታድየም ይደረጋል።

ተጠባቂው ፍልሚያ በኢቲቪ መዝናኛ እና በተለያዩ የዶትስትሪም አማራጮች በቀጥታ ይተላለፋል።

የዓመቱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ መድንን፤ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ መቐለ 70 እንደርታን በማሸነፍ ለፍፃሜው ጨዋታ ማለፋቸው ይታወሳል።

የታሪካዊው ዋንጫ የፍፃሜ  ጨዋታ ነገ ከረፋድ 5 ሰዓት ጀምሮ የሚደረግ  ሲሆን፤ ኢቢሲ የቅድመ ጨዋታ ትንታኔዎችን አካቶ ከረፋድ 4 ሰዓት ጀምሮ ወደ ተመልካቾች ይደርሳል።

እንድትከታተሉ እንጋብዛለን!

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: