በ23ኛው የዓለም ዋንጫ እጅግ ተጠባቂ በሆነው የሩብ ፍፃሜ መርኃ ግብር፣ ዛሬ ምሽት 4፡00 ሰዓት በሎስ አንጀለስ ስታዲየም የአውሮፓ ሻምፒዮኗ ስፔን ከቤልጂየም ጋር እጅግ አጓጊ ፍልሚያዋን ታደርጋለች።
በአሰልጣኝ ሉዊስ ዴ ላ ፎንቴ የምትመራው ስፔን በውድድሩ እስካሁን አንድም ጎል ባለማስተናገድ ብቸኛዋ ጠንካራ ቡድን ስትሆን፣ ግብ ጠባቂያቸው ኡናይ ሲሞን መረቡን ሳያስደፍር አዲስ ታሪክ እያስመዘገበ ይገኛል።
እነ ሮድሪ እና ፔድሪ በመሀል ሜዳ፣ እንዲሁም ላሚን ያማል እና ሚኬል ኦያርዛባል በፊት መስመር የቤልጂየምን ተከላካዮች ለመፈተን ተዘጋጅተዋል።
በአንጻሩ ባለፉት 18 ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት የማታውቀውና በሩዲ ጋርሲያ የምትመራው ቤልጂየም በማጥቃት ረገድ እጅግ አስፈሪ ሆና ቀርባለች።
በመጨረሻዎቹ ሦስት ጨዋታዎች ብቻ 12 ጎሎችን በማስቆጠር የውድድሩ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የሆነችው ቤልጂየም፣ ወሳኙ አማካያቸው አማዱ ኦናና በጉዳት ቢታጣም የኬቪን ደብሩይን ወደ መጀመሪያ አሰላለፍ መመለስ እና የጄረሚ ዶኩ ፍጥነት ልዩ ጥንካሬ ይሰጣታል።
ሁለቱ ሀገራት ከዚህ ቀደም 22 ጊዜ ተገናኝተው ስፔን የ12 ጊዜ የበላይነት ብትወስድም፣ ቤልጂየም በ1986ቱ የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ስፔንን በመለያ ምት አሸንፋ ማለፏ የሚዘነጋ አይደለም።
የዛሬውን ምሽት አስደናቂ ጨዋታ አሸናፊ በግማሽ ፍፃሜው ከፈረንሳይ ጋር የሚፋለም ይሆናል። በዚህ ጨዋታ ማን የሚያሸንፍ ይመስላችኋል? ግምታችሁን አጋሩን።
በዘረንቶስ ሰለሞን
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: