Search

አዲስ ቻምበር - በ13ኛው የዓለም የኢንዱስትሪዎች ትብብር ፎረም

ዓርብ ነሐሴ 09, 2017 101

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት (አዲስ ቻምበር) የሥራ ኃላፊዎች ከቱርክ እና ከሌሎች ሀገራት ባለሀብቶች ጋር የገበያ ትስስር ለመፍጠር በ13ኛው የዓለም የኢንዱስትሪዎች ትብብር ፎረም ላይ እየተሳተፉ መሆኑን አሳውቀዋል።
በአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ የተመራ ከ30 በላይ የንግድ ልዑካን ቡድን አባላት ትናንትና በቱርኪዬ ኢስታንቡል በተጀመረው ዓለም አቀፍ ፎረም ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የአዲስ ቻምበር ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ በተለይም ለኢቢሲ ዶትስትሪም እንደገለፁት፤ ፎረሙ ከቱርኪዬ እና ከሌሎች ሀገራት ባለሀብቶች ጋር የገበያ ትስስር ለመፍጠር ያግዛል።
በፎረሙ የተለያዩ አገራት ሚኒስትሮች እና በርካታ የንግድ ኩባንያ አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን፤ የሁለትዮሽ የንግድ ልውውጥን ለማሳደግ የሚረዱ ውይይቶች ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል።
ለፎረሙ ላይ አዲስ ቻምበርን ጨምሮ ከ1 ሺ 5ዐዐ በላይ ከቱርክ ከአፍሪካ እና ከተለያዩ አገራት የተውጣጡ በተለያዩ የንግድ ዘርፍ ላይት የተሰማሩ ተቋማት በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
 
 
በላሉ ኢታላ