Search

አዳማ ለከተማ ትራንስፖርት የሚውሉ 9 አውቶቢሶችን ተረከበች

ዓርብ ነሐሴ 09, 2017 133

ከከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የሚታየው የሕዝብ ቁጥር መጨመር የትራንስፖርት ፍላጎትን አሳድጎታል።
ይህን ፍላጎት ለማሟላት የተለያዩ የከተማ አውቶቡሶችን በመገጣጠም እና በማቅረብ ላይ የሚገኘው በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የቢሾፍቱ ሞተር ቪሂክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ዘጠኝ የከተማ አውቶቡሶችን ገጣጥሞ ለአዳማ ከተማ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አስረክቧል።
አውቶቡሶቹን ያስረከቡት የቢሾፍቱ ሞተር ቪሂክልስ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩኘ ም/ሥራ አስኪያጅ ሌተናል ኮሎኔል ሲሳይ ተሰማ ለትራንስፖርት ዘርፉን ልዩ ትኩረት በመስጠት ኢንዱስትሪው በቀን አንድ አውቶቡስ የማምረት አቅም ላይ መድረሱን ገልፀዋል።
አውቶቢሶቹን የተረከቡት የአዳማ ከተማ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የትራንስፖርት ዳይሬክተር አቶ ከበደ አዱኛ፤ በርካታ ነዋሪዎች ያሏት፣ የንግድ እና የቱሪዝም ከተማዋን የአዳማን የዕለት ተዕለት የትራንስፖርት እንቅስቃሴን ለማሳለጥ አውቶቡሶቹ አስፈላጊ መሆናቸውነ አንስተዋል።
ወደ ሥራ የሚገቡት አውቶቡሶቹ በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ከመገጣጠማቸው ባለፈ ምቹ እና ዘመናዊ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
 
 
በኤዶሚያስ ንጉሴ