ሰብዓዊነትን ማጠናከር እና ሰብዓዊ ሠራተኞችን ማክበር በሚል መሪ ሀሳብ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ቀን በኢትዮጵያ ተከብሯል።
በክብረ በዓሉ ላይ የእንግሊዝ እና የአሜሪካን አምባሳደሮችን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች በተገኙበት በኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማኅበር አማካኝነት ተከብሯል።
የኢትዮጵያ የቀይመስቀል ማኅበር ፕሬዝዳንት አበራ ቶላ የሰብአዊ ድጋፍ ለማድረግ ህይወታቸውን ያጡ ሰራተኞችን በማስታወስ በዓሉ እየተከበራ መሆኑን ገልፀው ማህበሩ ለሰብዓዊ ድጋፍ ለተጋለጡ ወገኖችን እያገዘ መሆኑን ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ደረን ዌልች ሁሉም ባለድርሻ አካላት በሰብዓዊ ጉዳይ ላይ የሚያደረገውን ጥረት አጠናክረው ሊያስቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ኤርቪን ማሲንጋ በበኩላቸው በዓለም ላይም ሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ ለችግር ተጋለጭ ለሆኑ ሰዎች የሚደረገውን ድጋፍ በቁርጠኝነት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርበት አመላክተዋል።
ዲፕሎማቶችን ጨምሮ የበዓሉ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማህበር እየሰራ ያለውን የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
በአሊ ደደፎ