የኤችአይቪ (ኤድስ) እና የቲቢ ምርመራ እና ሕክምና አገልግሎት መሻሻል ማሳየቱን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ አስታውቋል።
ከክልሉ ሁሉም ዞኖች የተውጣጡ የጤና ባለሙያዎች የተቀናጀ የቲቢ እና የኤችአይቪ (ኤድስ) ምርመራ እና ሕክምናን ለማጎልበት የሚያስችል ምክክር በታርጫ ከተማ አካሂደዋል።
በዚሁ ወቅት የቢሮው ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እንዳሉት፥ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች አገልግሎቱን ለማጠናከር እና ለማስፋት በማህበረሰብ አቀፍ ፕሮግራም የተቀናጀ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።

በዚህም በክልሉ በሚገኙ 44 የጤና ተቋማት አገልሎቱን ይበልጥ ለማጎልበት መቻሉን አቶ ኢብራሂም ጠቁመዋል።
ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች እና የሥራ ቦታዎች የጤና ተቋማትን የመገንባትና በዘመናዊ የሕክምና ግብዓቶች የማደራጀት ሥራም እየተከናወነ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
በክልሉ ከ200 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የኤችአይቪ (ኤድስ) ምርመራ ተደራሽ ማድረግ መቻሉ እና ቫይረሱ በደማቸው የተገኘባቸው 9 ሺህ 38 ዜጎች ተገቢውን ሕክምና እንዲከታተሉ መደረጉንም ጠቅሰዋል።
የቫይረሱን ከእናት ወደ ልጅ ስርጭት ለመግታትም በሁሉም የጤና ተቋማት ጥምር የምርመራ ሥርዓት ተዘርግቶ እየተሠራበት ይገኛል ብለዋል ኃላፊው።
የቲቢ ምርመራ ከተደረገላቸው 12 ሺህ 201 ዜጎች መካከል በሽታው የተገኘባቸው 3 ሺህ 789 ሰዎች መድሃኒት እንዲጀምሩ መደረጉም ተመላክቷል።
በሰለሞን ባረና
#ኢቢሲዶትስትሪም #ኢቲቪ #ኤችአይቪኤድስ #ቲቢ #ምርመራ #ሕክምና