Search

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ ሰፊ የመሠረተ ልማት ግንባታ እያከናወነ ያለው አፋር ክልል

ቅዳሜ ነሐሴ 10, 2017 108

በአፋር ክልል የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ ለሆቴል ኢንቨስትመንት ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ እንደሚገኝ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለፁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በሰመራ ከተማ በተገነባውና በርካታ ጎብኚዎችን የማስተናገድ አቅም ባለው “አፋር ያንጉዲ ሌግሪ ሆቴል” የምረቃ መርሐ-ግብር ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚህም፥ በክልሉ በሆቴል ኢንቨስትመንት ሀገር አቀፍ ኮንፍረንሶችን ለማዘጋጀት አቅም የፈጠሩ ትላልቅ ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

በ2018 ዓ.ም በሰመራ ከተማ የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረምን ለማዘጋጀት የኮሪደር ልማት እና የሆቴሎች ግንባታን ጨምሮ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አክለዋል።

የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ኢብራሂም ሁመድ በበኩላቸው በዘንድሮው ዓመት ብቻ ከ4 ሺህ 300 በላይ የውጭ ቱሪስቶች አፋርን መጎብኘታቸውን ጠቅሰው፤ በቀጣይ የጎብኚዎችን ቁጥር ለማሳደግ ለሆቴልና መስተንግዶ ዘርፍ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በክልሉ በኢንዱስትሪ እንዲሁም በሆቴልና መስተንግዶ ዘርፎች በርካታ ባለሀብቶች ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ መግባታቸውን የገለፁት ደግሞ የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ኤይሻ ያሲን ናቸው።

ይህም የክልሉን ገቢ በማሳደግ እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ለውጥ ማምጣቱን ነው ኃላፊዋ የተናገሩት።

በሁሴን መሐመድ

#EBCdotstream #ETV #Afar #Tourism