ዛሬ ቀጥሎ በተካሄደ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ዎልቭስን 4 ለ 0 በማሸነፍ ሊጉን በድል ጀምሯል።
የሲቲዝኞችን ግብ ራይንደርሰን፣ ሀላንድ እና ቼርኪ ከመረብ አሳርፈዋል።
በሲቲ አዳዲስ ፈራሚዎች ብቃት በታጀበው በዚህ ጨዋታ ቲጃኒ ሬንደርስ በመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታው የመጀመሪያዋን የሲቲ ግብ ሲያስቆጥር፤ ቼርኪ ለግሉ ቀዳሚውን ለሲቲ ደግሞ 4ኛውን ግብ አስቆጥሯል።
በሌላ በኩል ዎልቭስ ከጨዋታው መጀመር በፊት በቅርቡ በመኪና አደጋ ሕይወቱ ያለፈውን የቀድሞ ተጫዋቻቸው ዲያጎ ጆታን አስበዋል።
በሴራን ታደሰ