Search

በማዕከሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በራስ አቅም የተከናወነው የተሳካ የልብ ቀዶ ሕክምና

ቅዳሜ ነሐሴ 10, 2017 112

ለመጀመሪያ ጊዜ በውስጥ አቅም የተሳካ የልብ ቧንቧ ቀዶ ሕክምና ማከናወኑን የጅማ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ማዕከል አስታወቀ።

ለ4 ዓመት እንስት ህፃን የተደረገው የልብ ቧንቧ ቀዶ ሕክምና ውጤታማ እንደሆነ ለኢቢሲ ዶትስትሪም በማዕከሉ የደረት እና ልብ ቀዶ ሕክምና ‘ሰብ-ስፔሻሊስት’ ረዳት ፕሮፌሰር ዶ/ር ወርቅነህ ተስፋዬ በተለይ ለኢቢሲ ዶትስትሪም ገልፀዋል።

ከወሊድ በኋላ መዘጋት የሚገባው የደም ማስተላለፊያ ቧንቧ ክፍት በመሆኑ ምክንያት ያጋጠመ የጤና እክል እንደነበር ዶ/ር ወርቅነህ ተናግረዋል።

"የውጭ እገዛ ሳያስፈልግ በማዕከሉ የራስ አቅም የተከናወነው ቀዶ ሕክምና ለተቋሙ የከፍታ ጅማሮ፤ ለሀገሪቱ የጤና ዘርፍም ጨማሪ እሴት ነው" ሲሉ ገልፀዋል ዶ/ር ወርቅነህ።

ታካሚዋ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደምትገኝ ተናግረው፤ ለማዕከሉ ታሪካዊ በሆነው የልብ ቀዶ ሕክምና ላይ ተሳታፊ የነበሩ የሙያ ባልደረቦቻቸውን አመስግነዋል።

በአፎሚያ ክበበው

#ኢቢሲዶትስትሪም #ጅማዩኒቨርሲቲ #ሕክምናማዕከል #ልብሕክምና #ቀዶሕክምና