Search

ሥራ ከተሠራ፤ ሰው ባይመሰክር፣ ምድር ትመሰክራለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ቅዳሜ ነሐሴ 10, 2017 136

የአረንጓዴ ዐሻራ እና የኮሪደር ልማት ትስስር ለማህበረሰቡ አዲስ የአኗኗር ዘዬን እያላበሰ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የወላይታ ሶዶ ጉብኝታቸውን ተከትሎ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባጋሩት መልዕክት ነው።

ሰው በልማቱ ያገኘነውን ተጨባጭ ተጠቃሚነት አልተመለከትኩም ቢል እንኳ ምድሪቱ ትመሰክራለች ሲሉ የመጣውን ለውጥ ገልፀውታል።

በመተጋገዝ የሚታወቀው ትጉሁ የአካባቢው ማኅበረሰብ ከከተማ እስከ ገጠር ዘልቆ በተከናወነው የልማት ሥራ ላይ አሻራውን ማሳረፉን መስክረዋል።

በወላይታ ሶዶ እና አካባቢው በነበራቸው ቆይታ ማኅበረሰቡ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን እየተጠቀመ መመልከታቸውን ጠቅሰው፤ በምግብ ራስን ለመቻል የተከናወኑ ሥራዎች ሚዛን ደፊ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በሶዶ አቅራቢያ በግንባታ ላይ ያለው የአውሮፕላን ማረፊያ ለለውጥ ቅርብ የሆነውን የአካባቢውን ማኅበረሰብ እንቅስቃሴ የሚያሳልጠው መሆኑን አንስተዋል።

በጥሩ ሂደት ላይ ያሉት የኮሪደር ልማት እና የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራዎች ከግብ ሲደርሱ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚገለጥ ያላቸውን ፅኑ እምነትም ገልፀዋል።

በአፎሚያ ክበበው

#EBCdotstream #PMAbiyAhmed #WolaitaSodo #corridordevelopment #greenlegacy