የስፔን ላልጋ የመጀመሪያ ሳምንት መርሀ ግብሮች ዛሬም ቀጥለው ሲካሄዱ አትሌቲኮ ማድሪድ ከኤስፓኞል ምሽት 4:30 ላይ ይጫወታሉ።
የካታላኑ ተወካይ ኢስፓኞል በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከወራጆቹ በሁለት ነጥብ ብቻ ከፍ ብሎ በሊጉ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን አትሌቲኮ ማድሪድ ደግሞ ከሻምፒዮኑ ባርሴሎና በ12 ነጥብ ዝቅ ብሎ በ3ኛ ደረጃ አጠናቋል፡፡
በማናሎ ጎንዛሌዝ የሚመራው ኢስፓኞል በቅድመ ውድድር ዝግጅት ካደረጋቸው 6 ጨዋታዎች አራቱን አሸንፏል፡፡
ሁለቱ በድኖች ከተገናኙባቸው 56 ጨዋታዎች አትሌቲኮ 23ቱን በማሸነፍ የበላይነት አለው፡፡
ሴልታ ቪጎ ከ ሄታፌ እና አትሌቲክ ክለብ ከ ሴቪያ ሌሎች የዛሬ መርሀ ግብሮች ናቸው፡፡
በሴራን ታደሰ