Search

በለንደን ደርቢ ቼልሲ ከ ፓላስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

እሑድ ነሐሴ 11, 2017 95

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመርያ ሳምንት ዛሬ ቼልሲ ከክሪስታል ፓላስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
በ2024/25 በዋንጫ የታጀበ የውድድር አመት ያሳለፉት ሁለቱ ቡድኖች አዲሱን የውድደር አመት በድል ለመጀመር 10 ስአት ላይ ጨዋታቸውን ያርጋሉ፡፡
ቼልሲ ከፓላስ ባደረጋቸው ያለፉት 15 የሊግ ጨዋታዎች ያልተሸነፈ ሲሆን ዛሬም የበላይነቱን ለማስቀጠል ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡
በስታምፎርድ ብሪጅ በሚደረገው ጨዋታ ሌቪ ኮልዊል በጉዳት ኒኮላስ ጃክሰን ደግሞ በቅጣት የማሰለፉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡ በመርሀ ግብሩ ጃኦ ፔድሮ በቋሚነት እንደመሰለፍ ይጠበቃል፡፡
በሌላ መርሀ ግብር ኖቲንግሃም ፎረስት ከብሬንትፎርድ በተመሳሳይ 10 ሰዓት ይጫወታሉ።
 
በሴራን ታደሰ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ተያያዥ ዜናዎች: