የመጀመርያው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በሚደረግ አንድ ጨዋታ ይጠናቀቃል፡፡
በዚህ አመት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የተመለሰው ሊድስ ዩናይትድ ምሽት 4 ሰአት ላይ ከኤቨርተን ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
በኢላንድ ሮድ በሚደረገው ጨዋታ አዲሱ የሊድስ አጥቂ ዶሚኒክ ካልቨርት ሌዊን የቀድሞ ክለቡን ኤቨርተን በተቃራኒ የሚገጥም ይሆናል፡፡
የ28 አመቱ አጥቂ ለ9 አመታት ካሳለፈበት ኤቨርተን በቅርቡ መለያየቱ የሚታወስ ነው፡፡
በኤቨርተን በኩል ጃርድ ብሬዝዌት ባጋጠመው ጉዳት እንደማይሰለፍ ተረጋግጧል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ