የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በአፋር ክልል፣ ሰመራ ከተማ አረንጓዴ ዐሻራን ጨምሮ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አከናውነዋል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፥ ሚኒስቴሩ እና ተቋማቱ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎታቸው 11 የአቅመ ደካሞች ቤቶችን በአዲስ ከመተካት በተጨማሪ ለክልሉ አንድ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ይገነባሉ ብለዋል።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በኢትዮጵያ በየዓመቱ በክረምት ወቅት የሚከናወነው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለዘመናት የቆየውን የኢትዮጵያውያን የመደጋገፍ ባህልን የሚያጠናክር ነው ሲሉ ገልፀዋል።
የክረምት በጎ ፍቃድ ሥራዎች በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ሥራም በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
አረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ እና የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍን ጨምሮ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት በተከናወኑበት መርሐ-ግብር የትራስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የሰመራ ከተማ ማህበረሰብ ተሳትፈዋል።
በሁሴን መሀመድ
#ኢቢሲ #ኢቢሲዶትስትሪም #አፋር #በጎፈቃድ #አገልግሎት