Search

ጋናዊው ተጫዋች ላይ የዘረኝነት ጥቃት ያደረሰው ግለሰብ ታገደ

Aug 18, 2025

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ ጨዋታ የቦርንማውዙ አማካይ አንትዋን ሴሜኒዮ ላይ የዘረኝነት ጥቃት ያደረሰው ግለሰብ ከእግር ኳስ ታግዷል፡፡
ባለፈው አርብ ሊቨርፑል ከ ቦርንማውዝ ባደረጉት ጨዋታ ጋናዊው አማካይ በቆዳ ቀለሙ ምክንያት በደረሰበት ዘለፋ ጨዋታው 29ኛው ደቂቃ ላይ ለተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ድርጊቱን የፈጸመው የ47 አመቱ የሊቨርፑል አካባቢ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ ሲደረግበት ቆይቷል፡፡
ግለሰቡም ከዚህ በኋላ በየትኛውም እግር ኳስ ሜዳ እንዳይገኝ እና በተጨማሪም ከስቴዲየሞች ከ1.6 ኪሎሜትር ርቀት በታች እንዳይጠጋ ተወስኖበታል፡፡
ሊቨርፑል 4 ለ 2 ባሸነፈበት ጨዋታ ሴሜኒዮ ሁለት ግቦችን ማስቆጠሩም ይታወሳል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ