ቶተንሀም ሆትስፐር የተከላካዩን ክርስቲያን ሮሜሮ ውል አራዝሟል፡፡
አርጀንቲናዊው የመሀል ተከላካይ በሰሜን ለንደኑ ክለብ ለቀጣይ አራት አመት የሚያቆየውን ውል አራዝሟል፡፡
በ2021 ከአታላንታ ወደ ቶተንሀም ያመራው የ27 አመቱ ተጫዋች ከሶን ሂዩንግ ሚን በኋላ የክለቡ አምበል ሆኖ መመረጡም ይታወቃል፡፡
በክለቡ መለያ 129 ጨዋታዎችን ያደረገው ክርስቲያን ሮሜሮ እስከ 2029 ከቶተንሀም ጋር የሚቆይም ይሆናል፡፡
በሀብተሚካኤል ክፍሉ