Search

ዳያስፓራው በሕዳሴ ግድብ ያሳየውን ግንባር ቀደም ተሳትፎ በምክክሩም ሊደግመው ይገባል - ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (ዶ/ር)

Aug 18, 2025

ዳያስፓራው ማኀበረሰብ በሕዳሴው ግድብ ግንባታ ያደረገውን ግንባር ቀደም ተሳትፎ በሀገራዊ ምክክሩም ሊደግመው እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ (/ር) ገልጸዋል።  

ዳያስፓራው ማኀበረሰብ ምንጊዜም ለሀገሩ ቀናኢ የሆነ ሃሳብ እንዳለው አንስተው፤ ይህን ተግባር በሀገራዊ ምክክር ተሳትፎም ማጠናከር እንደሚገባ አመላክተዋል።

ለሀገር ግንባታ በግንባር ቀደምትነት የቆመ ዳያስፖራው በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብ ሒደት  በንቃት መሳፉንም አስታውሰዋል።

በደቡብ አፍሪካ የተካሄደው  የሀገራዊ ምክክር ሂደት ኢትዮጵያውያን  የውጪ ጣልቃ ገብነት ሳያስፈልግ ችግሮቻችንን በእራሳችን መንገድ መፍታት እንደምንችል  ያረጋገጥንበት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ የሀሳብ ፣የአመለካከት እንዲሁም የፓለቲካ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ በምክክር መፍታት እንደሚቻል ያየንበት አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ነበር ሲሉ ገልፀዋል።

በአጀንዳ ማሰባሰብ ሒደቱ ዳያስፖራው ማኀበረሰብ ለሀገር ግንባታ እና ለዘላቂ ሰላም ምን ያህል ጉጉት እንዳለው ማየት ተችሏል ብለዋል።

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስለ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያላቸው ግንዛቤ መጨመሩ በጥሩ መግባባት እና ውይይት ችግሮች ለመፍታት ይረዳል ሲሉም አንስተዋል።

የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት እና በመካከለኛው ምስራቅ ተደራሽነት እንዲኖረው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ሲሉም አስታውቀዋል።

በተመሳሳይ በተለያዩ ሀገራት ከሚገኙ ዳያስፖራዎች ጋር ቀጣይ ውይይቶች እንደሚካሄዱ አንስተው፤ በዚያም የነቃ ተሳትፎ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል።

 

 

በሄለን ተስፋዬ