Search

ማንቸስተር ሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ በቀረቡበት የፋይናንስ ደንብ ጥሰት ክሶች ጥፋተኛ ተባለ

ዓርብ መስከረም 15, 2019 111

ማንቸስተር ሲቲ ከፕሪሚየር ሊጉ የፋይናንስ ደንቦች ጋር በተያያዘ ከቀረቡበት 115 ከባድ ክሶች ውስጥ በአብዛኛዎቹ ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

ገለልተኛው አጣሪ ኮሚሽን ባደረገው ምርመራ ክለቡ ከቀረቡበት 115 ክሶች ውስጥ በአንዱ ብቻ ነፃ ሲባል፣ በቀሩት 114ቱ ላይ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል።

ይሁን እንጂ በክለቡ ላይ የሚጣለው ቅጣት እስካሁን ያልተወሰነ ሲሆን፣ ማንቸስተር ሲቲም በውሳኔው ላይ ይግባኝ እንደሚጠይቅ ይጠበቃል።

ይህ ከፍተኛ ውዝግብ ያስነሳው ክስ መነሻውን ያደረገው ክለቡ እ.አ.አ ከ2009 እስከ 2018 ባሉት ዓመታት ትክክለኛ የፋይናንስ መረጃዎችን፣ የተጫዋቾች እና የአሰልጣኞችን ትክክለኛ የክፍያ ዝርዝር አለማቅረቡ እንዲሁም የሊጉን ደንብ (PSR) ጥሷል በሚል በየካቲት 2023 የቀረበበት ክስ ነው።

ማንቸስተር ሲቲ እስካሁን ክሶቹን ሲያስተባብል የቆየ ሲሆን፣ አሁንም የዳኝነት ሂደቱ ገና አለመጠናቀቁን እና በጉዳዩ ላይ ይግባኝ ለመጠየቅ ዝግጁ መሆኑን አመልክቷል።

በክለቡ ላይ የሚጣሉ ቅጣቶች ደረጃ ገና ባይወሰንም፣ እንደ ፕሪሚየር ሊጉ ሕጎች  ከሆነ ቅጣቱ ከከባድ የገንዘብ መቀጮ እስከ ከፍተኛ የነጥብ ቅነሳ፣ ያሸነፏቸውን ዋንጫዎች እስከ መነጠቅ አልፎም ከሊጉ እስከ ማሰናበት ሊደርስ እንደሚችል ተጠቁሟል።

በዘረንቶስ ሰለሞን

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: