Search

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ በሱዳን 1 ለ 0 ተሸነፈች

ዓርብ መስከረም 15, 2019 109

ኬኒያ፣ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ በጋራ ለሚያስተናግዱት የ2027 አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በማጣሪያው የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሱዳን 1 ለ 0 ተሸንፏል።

በደቡብ ሱዳን ጁባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ በረከት ሳሙኤል የሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ሙሐመድ ዒሳ 86ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሮ ሱዳን ሙሉ ሦስት ነጥብ ይዛ እንድትወጣ አስችሏል። 

በተመሳሳይ ሰዓት ሞዛምቢክ ከ ሴኔጋል ያደረጉት የምድብ 10 ሌላኛው ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል።

ውጤቱን ተከትሎ ሱዳን ምድቡን በሦስት ነጥብ መምራት ጀምራለች።

ዋልያዎቹ 2ኛ የማጣሪያ ጨዋታቸውን በቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋሉ።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: