አርሰናል ኤቤሬቺ ኤዜን ከክሪስታል ፓላስ ማስፈረሙን አስታውቋል፡፡
ኤቤሪቺ ኤዜ በመድፈኞቹ ቤት 10 ቁጥር መለያ የሚለብስ ሲሆን፤ ከክለቡ ጋርም የአምስት ዓመት ውል ተፈራርሟል፡፡
ከካይ ሀቨርዝ ጉዳት በኋላ የኤዜን ዝውውር በፍጥነት ያከናወነው አርሰናል፤ ለእንግሊዛዊው ተጫዋች 67 ሚሊዮን ፓውንድ መክፈሉ ተነግሯል፡፡
ኤቤሬቺ ኤዜ በክረምቱ የዝውውር መስኮት የአሰልጣኝ ሚካኤል አርቴታ 7ኛው ፈራሚም ሆኗል፡፡
አርሰናል ምሽት 1:30 ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ከሊድስ ዩናይትድ ጋር የሚያደርግው ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ