በ2ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሜዳው ከሊድስ ዩናይትድ የተጫወተው አርሰናል 5 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በኢምሬትስ በተደረገው ጨዋታ ዩሪያን ቲምበር ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ቪክቶር ጊዮኬሬሽም በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል፡፡ ቡካዮ ሳካ ቀሪዋን ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች ነው፡፡
ሁለት ግብ አስቆጥሮ አንድ ለግብ የሚሆን ኳስ ያመቻቸው ቲምበር ከናቾ ሞንሪያል በኋላ ለሦስት ግቦች መገኝት ምክንያት የሆነ ተከላካይ ሆኗል፡፡
60 ሺ ተመልካቾች በታደሙበተ ጨዋታ አምበሉ ማርቲን ኦዴጋርድ እና ቡካዮ ሳካ ጉዳት አጋጥሟቸው ከሜዳ ለመውጣት ተገደዋል፡፡
እንግሊዛዊው አማካይ ማክስ ዶውማን ተቀይሮ በመግባት የመጀመርያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታውን ያደረገ ሲሆን ከኢታን ንዋኔሪ እና ጀርሚ ሞንጋ በመቀጠል 16 አመት ሳይሞላው በሊጉ የመሰለፍ እድል ያገኝ በእድሜ ትንሹ 3ኛው ተጫዋች ሆኗል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ