የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና የቱሪዝም መዳረሻ እና የንግድ ማዕከል ወደሆነችው የሞዛምቢኳ ናካላ ከተማ በሳምንት ሦስት ጊዜ የሚደረግ አዲስ የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት መጀመሩን አስታወቀ።
ዛሬ ጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው ይህ አዲስ የበረራ መስመር፣ በኢትዮጵያ እና በሞዛምቢክ መካከል ያለውን አህጉራዊ ትሥሥር ይበልጥ የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ ለቀጠናው የቱሪዝም እና የቢዝነስ ዕድገት የላቀ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል።
የበረራ መስመሩ አየር መንገዱ በአፍሪካ አህጉር ያለውን ተደራሽነት ከማስፋፋቱም ባሻገር፣ ነጋዴዎች እና ቱሪስቶች በቀላሉ የመንቀሳቀስ ዕድል እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑ ተጠቅሷል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: