የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሦስተኛውን የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ አስመልክቶ ከአፍሪካ ሀገራት የሚዲያ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
ሚኒስትሩ በውይይቱ ወቅት፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል ስላለው አጋርነት እና የትብብር ዘርፎች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚህም የሩሲያ መንግሥት የአፍሪካ ሀገራት ከኒውክሌር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንደ ኢትዮጵያ ካሉ ሀገራት ጋር በትብብር እየሠራች መሆኗን አስታውቀዋል።
ሩሲያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የመሠረተችው ግንኙነት በመከባበር፣ በጋራ ተጠቃሚነት እና በሀገራቱ ፍላጎት እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅም ላይ የተመሠረተ መሆኑን አብራርተዋል።'
ከኢትዮጵያ ጋር በኒውክሌር ልማት ዘርፍ በተጀመረው ትብብር የኢትዮጵያውያንን ባለሙያዎች አቅም ማሳደግ ዋነኛ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፣ ሩሲያ በኒውክሌር ልማት ዘርፍ ያላትን ልምድና አቅም ለኢትዮጵያ ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲሳካና በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ሩሲያ ፍላጎት እንዳላት ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በማህሌት ታደለ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: