Search

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ16 ሀገራት አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ዛሬ ይቀበላሉ

ማክሰኞ ኅዳር 08, 2019 166

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በኢትዮጵያ አዲስ የተሾሙ የ16 ሀገራት አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ዛሬ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይቀበላሉ።

በመርሐ ግብር ከአፍሪካ፣ ከእስያ፣ ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከአውሮፓ እና ከካሪቢያን ሀገራት የተወከሉ ተሿሚ አምባሳደሮች በክብር ዘብና በማርሽ ባንድ ሥነ ሥርዓት ታጅበው ደብዳቤያቸውን ያቀርባሉ።

የሹመት ደብዳቤያቸውን ከሚያቀርቡት መካከል የሰሜን ኮሪያ አምባሳደር ሶንግ ኢል ሂዮክ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አምባሳደር አብዱላህ ሀሰን ኡበይድ ሀሰን አልሻምሲ፣ የቆጵሮስ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሳቫስ ቭላዲሚሩ፣ የቼክ ሪፐብሊክ አምባሳደር ያን ሩቼክ እና የአየርላንድ አምባሳደር ኪያራን ማደን ይገኙበታል።

እንደዚሁም የህንድ፣ የቻድ ሪፐብሊክ፣  የኦስትሪያ፣ የኖርዌይ፣ የፊንላንድ ሪፐብሊክ የማልታ ሪፐብሊክ፣ ጣሊያን፣ የባርቤዶስ እና ደቡብ ኮሪያ አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዚዳንት ታዬ ያቀርባሉ።

በሳዳት መሀመድሳኒ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: