የኢትዮጵያ ጥራትና ሽልማት ድርጅት 13ኛውን ዙር ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ሥነ-ሥርዓት፣ ኅዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም በታላቁ ቤተ መንግሥት እንደሚያካሂድና ለዚህም ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
ድርጅቱ በምርትና አገልግሎት ጥራት የላቀ ውጤት ያመጡ ተቋማትን እንደሚያበረታታ በመግለጽ፣ በዚህኛው ዙር ከተመዘገቡት 71 ተቋማት ውስጥ 58ቱ የምዘና ሂደቱን ማጠናቀቃቸውን ጠቁሟል።
የላቀ ውጤት ካመጡ ተቋማትም ውስጥ 37ቱ በአምራች፣ 13ቱ በአገልግሎት፣ 10ሩ በጤና፣ 7ቱ በፐብሊክ ሰርቪስ እና 4ቱ በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ናቸው።
የዘንድሮውን ውድድር ልዩ የሚያደርገው ደግሞ የማወዳደሪያ መስፈርቱ ለአራተኛ ጊዜ መከለሱ ነው።
ይህ ክለሳ የኢትዮጵያ ዲጂታል 2030 ዕቅድን፣ ተኪ ምርቶችን፣ የዓለም አቀፍ የልህቀት ሞዴሎችን እንዲሁም የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) አጠቃቀምን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።
የጥራት ሽልማቱ ምርትና አገልግሎቶች መስፈርቶችን አሟልተው እንዲቀርቡ ከማድረግ ባለፈ፣ የተጠቃሚውን እርካታ ለማረጋገጥ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ለማጠናከር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ እንደሆነ ተመላክቷል።
የአሸናፊዎች ስም ዝርዝርና ደረጃ በዕለቱ ይፋ ተደርጎ፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዜና ቻናል በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል።
በመቅደስ እንዳለ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: