Search

በትግራይ ክልል የደረሰ ሰብል የመሰብሰብ ዘመቻ እየተካሄደ ነው

ቅዳሜ ኅዳር 19, 2019 115

የራያ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞች እና ተማሪዎች በትግራይ ክልል፣ እንዳመኾኒ ወረዳ፣ በሕዝባ ተክለሃይኖት እና በመስዋእቲ ቀበሌዎች ለአቅመ ደካማ አርሶ አደሮች የደረሰ ሰብል ሰብስበዋል።

ከ350 በላይ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አባላት በተሳተፉበት ዘመቻ 15 ሄክታር መሬት ላይ ያለ ሰብል ታጭዷል።

በዚህም 45 ሴቶችን ጨምሮ 60 አቅመ ደካማ የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል።

ዘመቻው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሰብሉ ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት በመከላከል ምርትን ለማዳን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል።

ራያ ዩኒቨርሲቲ ከማኅበረሰቡ ጋር በመተባበር የሚያከናውናቸውን የሥራ ዘመቻዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተመላክቷል።

በአስማረ ብርሃኑ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: