Search

ኪን ኢትዮጵያ በሞስኮ የኢትዮጵያን ባህል እና ኪነጥበብ እያስተዋወቀ ይገኛል

እሑድ መስከረም 04, 2018 31

የኪን ኢትዮጵያ የባህል እና የጥበብ ቡድን ሁለተኛውን የጥበብ ድግስ በሩሲያ ሞስኮ ከተማ እያቀረበ ይገኛል።
ኢትዮጵያን የማንሰራራት ብስራት በጥበብ እያበሰረ የሚገኘው እና ከ65 በላይ ልዑክ ይዞ ወደ ሩሲያ ያቀናው ቡድኑ፤ የዛሬውን የመድረክ ትዕይንት እያቀረበ ያለው በእውቁ የፊልሃርሞኒክ ራችማኒኖፍ ኮንሰርት አዳራሽ ነው።
 
የኪን ኢትዮጵያ የባህል እና የጥበብ ቡድን በሴንት ፒተርስበርግ በነበረው የመድረክ ትዕይንት በታዳሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኘ ሲሆን፤ በዛሬው የሞስኮ የመድረክ ዝግጅትም በርካታ ታዳሚዎችን እያዝናና የኢትዮጵያን ባህል በማስተዋወቅ ላይ ነው።
በዝግጅቱ ላይ የኢትዮጵያ ባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነፊሳ አልማህዲን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
የዛሬው የኪን ኢትዮጵያ የመድረክ ዝግጅት በሩሲያ ቆይታው የመጨረሻው ዝግጅቱ ነው።
በቀጣይ ወደ ሌሎች የዓለም ክፍሎች በማቅናት የኢትዮጵያን ባህል፣ ቋንቋ እና እሴት የሚያስተዋውቅ ይሆናል።
 
በፍሬው በኩረጽዮን