በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እጅግ የተጎሳቆሉ ቤቶችን በማፍረስ የተገነቡ 253 ቤቶችን የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚገባቸው የሀገር ባለውለታዎች፣ ሀገር ሲያገለግሉ ለማህበራዊ ችግር ለተጋለጡ የአልጋ ቁራኛዎች፣ ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ማስተላለፋቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
“ባለፈው እሁድ ያስተላለፍናቸውን ጨምሮ በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ ከገነባናቸው ከ3 ሺህ በላይ ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 924 የሚሆኑትን የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚገባቸው ወገኖቻችን አስተላልፈናል” ብለዋል ከንቲባዋ።

ቤቶቹ የጸዱ፣ መሠረታዊ ግብዓቶች የተሟሉላቸው፣ ዘመናዊ እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን የሚፈጥሩ፣ የራሳቸው ቅጥር ግቢ እና የጋራ መገልገያዎች ያሏቸው፣ የህፃናት መዝናኛና መጫወቻ እንዲሁም የንግድ ሱቆችን ያካተቱ መናቸውንም ነው የገለጹት።
የበጎ ፈቃድ ተግባሩን ለደገፉ ልበ ቀናዎች እና ላስተባበሩ የከተማዋ አመራሮች በሙሉ ከንቲባ አዳነች በተጠቃሚዎች ስም ምስጋና አቅርበዋል።