እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ።
የመስቀል በዓል እንደገና የመገለጥና እንደገና የማንሣት በዓል ነው። መስቀሉ ከ300 ዓመታት በላይ ተቀብሮ ነበር። የጠፋና የተረሳ፤ ያለቀና የደቀቀ መስሎ ነበር።
ከዘመናት በኋላ ግን ብርቱ መሪ ሲያገኝ ደመራው ተደምሮ፣ ተራራው ተቆፍሮ እንደገና ወጣ። እንደገና ተገለጠ።
ይህ ለኢትዮጵያም የሚሠራ ነው። እንደገና ትነሣለች፣ እንደገና ታበራለች። እንደገናም ለዓለም ትገለጣለች።
መልካም የደመራና የመስቀል በዓል ይሁንልን።