በኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል አከባበር ወቅት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በርካታ ህዝብ የሚታደምበት እና አባገዳዎች፣ ሀደ ስንቄዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙበት የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል መስከረም 24 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይከበራል፡፡
በዓሉ በሠላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ትኩረት ሰጥተው ወደ ተግባር በመግባት እየሰሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጾ÷ በተለይ በዓሉ ወደሚከበርበት ስፍራ የሚመጡ ታዳሚዎች ለጋራ ደህንነት ሲባል ፍተሻ መኖሩን ተገንዝበው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡
ከዚህ ቀደም የተከበሩ ኃይማኖታዊና ብሔራዊ በዓላት በሠላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር ወሳኝ ስራ ማከናወኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውሷል።
የዘንድሮው የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል በሠላም እንዲከበር የበዓሉ ታዳሚዎች እና የከተማው ነዋሪ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ በፀጥታ አካላት ስም ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
በመሆኑም የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል ተከብሮ እስከሚጠናቀቅ፦





፨ ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ፣










ከመስከረም 23 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ አስታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ዙሪያ ከሚገኙ የሸገር ከተማ አካባቢዎች በርካታ ህዝብ በዓሉን ለማክበር ከዋዜማው ጀምሮ ወደ ከተማችን የሚገባ በመሆኑ መላው ህብረተሰብ ተገቢውን አክብሮት በመስጠት የእንግዳ ተቀባይነት እሴታችንን አጉልቶ ሊያሳይ እንደሚገባ ፖሊስ አስታውሶ፤ በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያ እና በአካባቢው በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ገልጿል፡፡
በመጨረሻም ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-26-43-59 ፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አስተላልፏል፡፡