Search

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ ኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በድምቀት እንዲከበር ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ

ቅዳሜ መስከረም 24, 2018 130

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ ኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በድምቀት እንዲከበር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የክልሉ ፕሬዚዳንት ሽመልስ ባስተላለፉት መልዕክት፥ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የኢሬቻ ሆረ ፊንፊኔ በዓል እንግዶችን በመቀበልና በማስተናገድ ላሳዩት ትብብርና ፍቅር አመስግነዋል፡፡
የኦሮሞን ሕዝብ ደስታ ለመጋራት በበዓሉ ላይ ለታደሙ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ተወካዮች ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ነው ያሉት፡፡
በተመሳሳይ በዓሉ በድምቀት እንዲከበር ላደረጉ የጸጥታ አካላት እንዲሁም ባህሉን ለዓለም ለማሳየት እገዛ ላደረጉ የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙሃን ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የኢሬቻ በዓልን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) እንዲመዘገብ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡