ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከከፍተኛ አመራሮች ጋር የገጠር ኮሪደር ስራዎች ላይ ባደረጉት ውይይት፤ ከፍተኛ የቤት ችግር ስላለ እሱን ለመቅረፍ እየተሰራ ነው ብለዋል።
የቤት ችግር ከመቅረፍ ባለፈ የዜጎችን ኑሮ የሚያዘምን አሰራር መተግበር እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።
መንግሥት በሚቀጥሉት ዓመታት ከ1.5 ሚሊዮን ያላነሱ ቤቶችን ለመገንባት አቅድ ማስቀመጡን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህም በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በክልሎችም ጭምር የሚተገበር መሆኑን አመልክተዋል።
በዘርፉ ያለውን አቅም ለማጎልበት የ3ዲ ቤት አገነባብ ቴክኖሎጂን ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል።
በአነስተኛ ወጪ ከአካባቢ በሚገኙ ግብዓቶች የተሻለ መኖሪያ ለመገንባት የሚደረገው ጥረት ለገጠሩ ማኅበረሰብ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለዉ ጠቁመዋል።
በአጭር ጊዜ ዉስጥ በሀገር ደረጃ ትልቅ ዉጤት ለማምጣትና የዜጎችን የቤት ችግር ለመቅረፍ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡
በቢታንያ ሲሳይ
#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #AbiyAhmedAli #house #RuralCorridors