Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከምባታ እና በሀላባ ዞኖች 200 ተጨማሪ ሞዴል የገጠር ቤቶች እንዲገነቡ ተልዕኮ ሰጡ

ሓሙስ መስከረም 29, 2018 74

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለከምባታ እና ለሀላባ ዞኖች ነዋሪዎች እና አመራሮች እንዲሁም በጎ ልብ ላላቸው በሙሉ የመንግሥት ድጋፍ ሳይታከልበት በዞኖቹ አቅም እና በህዝብ ትብብር በሁለቱ ዞኖች በድምሩ 200 ተጨማሪ ሞዴል የገጠር ቤቶች እንዲገነቡ ተልዕኮ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሀላባ እና በከምባታ ዞኖች የተገነቡ ሞዴል መንደሮችን ባስረከቡበት ወቅት፥ አርሶ አደሮችን፣ የከተማ ነዋሪዎችን እንዲሁም ባለሃብቶችን አስተባብረን በዚህ ዓመት በሁለቱ ዞኖች ሞዴል የገጠር ቤቶችን ቁጥር 200 ብናደርስ፣ ጅማሮው እየሰፋ ይሄዳል ብለዋል።

ይህን መልካም ተሞክሮ በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ ወደ 1 ሺህ ቤቶች ብናሳድገው፤ በዚያ መንገድ እየተበራከተ የበርካታ ዜጎችን ሕይወት የሚነካ ይሆናል ነው ያሉት።

ሁሉም አመራር እና ኅብረተሰቡ ተልዕኮውን ወስደው በትብብር ከፈፀሙ እንደሚያሳኩት እርግጠኛ ነኝ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የሁለቱ ዞኖች አመራሮች ማኅበረሰቡን አስተባብረው ሞዴል የገጠር ቤቶችን ቁጥር 200 ማድረስ ከቻሉ ተመልሰው መንደሮቹን እንደሚጎበኙ ቃል ገብተዋል።

በመሐመድ ፊጣሞ

#ebcdotstream #modelruralvillages #ሞዴልየገጠርመንደሮች #pmabiyahmed