Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለስልጤ ዞን እና ለሀዲያ ዞን አመራሮች ተልዕኮ ሰጡ

እሑድ ጥቅምት 02, 2018 191

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በስልጤ እና በሀዲያ ዞኖች ከወረዳ ጀምሮ ላሉ አመራሮች ተልዕኮ ሰጥተዋል።

ተልዕኮው አመራሮቹ በመጪዎቹ ወራት ዞኖቹ ያላቸውን ሀብት በመጠቀም ብሎም የአካባቢዎቹን ተወላጆች በማስተባበር በእያንዳንዱ ዞን 1 ሺህ ሞዴል የገጠር መኖሪያ ቤቶች እንዲገነቡ የሚጠይቅ ነው።

መንግሥት የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ 1.5 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የቀረጸው ፕሮጀክት ከተሞችን ብቻ የሚመለከት እንዳልሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልጸዋል።

በመጪው ምርጫ ለወረዳ፣ ለዞን፣ ለክልል እና ለፌደራል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ የስልጤ ዞን እና የሀዲያ ዞን እጩዎች ይህን ካልተገበሩ መመረጥ የለባቸውም ሲሉ ጠቁመዋል።

ተመራጮች ሠርተው ባሳዩት እንጂ እንሠራለን ብለው ቃል በሚገቡት ኃላፊነት ላይ ሊቀመጡ እንደማይገባም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያመላከቱት።

ከትናንት በስቲያ ርክክባቸው የተፈጸመ የሀዲያ ዞን እና የስልጤ ዞን ሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታ 3 ወራት ብቻ መውሰዱን ጠቅሰው፤ እስከ ምርጫው ያለው ጊዜ የእስከአሁኑን እጥፍ ውጤት ለማስመዝገብ በቂ መሆኑን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ተልዕኮውን በሰጡበት መልዕክታቸው ይህ ተግባር ሳይፈጸም አካባቢዎቹን ተመልሰው እንደማይጎበኙም ተናግረዋል።

በአፎሚያ ክበበው

#ebcdotstream #ethiopia #AbiyAhmedAli #ruralcorridors #modelvillages #smartvillages