31ኛውን ኮፕ ለማዘጋጀት ጥያቄ አቅርበው በሂደት ላይ ያሉት ቱርኪዬ እና አውስትራሊያ 32ኛውን ኮፕ ለማዘጋጀት ኢትዮጵያ በመመረጧ ደስታቸውን ገልጸዋል።
በብራዚል ቤሌም እየተካሄደ ከሚገኘው 31ኛው የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ ጎን ለጎን የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ከሀገራቱ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅትም 31ኛውን ኮፕ ለማዘጋጀት ጥያቄ አቅርበው በሂደት ላይ ያሉት ቱርኪዬ እና አውስታራሊያ ኢትዮጵያ አፍሪካን በመወከል ኮፕ 32ን ለማሰናዳት በመመረጧ፣ እንኳን ደስ አላችሁ ማለታቸውን ተናግረዋል።
ሀገራቱ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ተግባራዊ እርምጃ በመውሰድ ላሳየችው ቁርጠኝነት እና ላገኘችው ውጤት እውቅና እንደሚሰጡ መናገራቸውን ነው ሚኒስትሯ ለኢቢሲ የተናገሩት።
በቀጣይም ኮፕ 31 የተሻለ እና ስኬታማ እንዲሆን ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር በትብብር እንደምትሠራ ማረጋገጣቸውንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
በሀብታሙ ተክለስላሴ
#ebcdotstream #cop30 #Ethiopia #Turkiye #Australia