Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፊንላንድ ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር ተወያዩ

ቅዳሜ ኅዳር 13, 2018 73

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፊንላንድ ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ስተብ ጋር በቀጠናዊ፣ ባለብዙ ወገን ትብብር፣ እና በሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በትምህርት፣ በአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ እና በኢትዮጵያ በተከፈተው የኢኮኖሚ ምኅዳር ስላሉ የኢንቨስትመንት እድሎች ተወያይተናል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው እንዳሰፈሩት፤ ውይይታችን የሁለትዮሽ ትስስራችንን እና የጋራ ጥቅም ትብብሮችን በማጠናከር ላይ ያለንን አቋም ያጠናከረም ነበር ሲሉ ገልፀዋል።