Search

ለብሔራዊ ጥቅሞች መጠበቅ ወሳኝ የሆነው የጋራ ጥረት

ማክሰኞ ኅዳር 16, 2018 59

የሀገርን ህልውና በፅኑ መሰረት ላይ ለማቆም፣ እንደ አረም የበቀሉ የተዛቡ ትርክቶችን በማረም የአንድነትን ማገር ማጥበቅ እንደሚያስፈልግ በርካቶች ይገልጻሉ።
የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎችም፣ በተዛባ ትርክት የተፈጠሩ ልዩነቶችን በማጥበብ እና ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር፣ ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ በጋራ መሥራት እንደሚገባ ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።
ኢቲቪ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት፤ በተለያዩ ጊዜያት በሀገሪቷ ለተከሰቱ አለመግባባቶች ዋነኛ መንስኤ የነጣጣይ ትርክቶች ተፅዕኖ መሆኑን ገልፀዋል።
ነጣጣይ ትርክቶች ልዩነትን በማንገስ፣ ችግር ከመፍጠር ባለፈ ብሔራዊ ጥቅምን የሚያሳጡና አክሳሪ መሆናቸውንም ነዋሪዎቹ አንስተዋል።
ስለሆነም ኢትዮጵያውያን የተዛቡ ትርክቶችን በማረምና ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ለብሔራዊ ጥቅሞች በጋራ መሥራት እንደሚገባቸው አመላክተዋል።
አያይዘውም፤ የነጣጣይ ትርክቶችን ዘርፈ ብዙ ጉዳቶች በተገቢው መንገድ በመገንዘብ፣ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጎሉና ሕዝብን አሰባሳቢ በሆኑ የጋራ ትርክቶች ላይ ማተኮር እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያውያን አንድነታቸውን በማጠናከር እንደ ሀገር የሚታዩ ዕድሎችን መጠቀም አለባቸው ያሉት ነዋሪዎቹ፤ ዜጎች ለብሔራዊ ጥቅሞች መጠበቅ በጋራ ሊቆሙ እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
 
በተስፋሁን ደስታ