ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ መክፈቻ ጨዋታ መሰለፍ እንደሚፍል ይፋ ሆኗል።
የወቅቱ የአል ናስር አጥቂ በዓለም ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ፖርቹጋል ከ አየርላንድ ሪፐብሊክ በነበራት ጨዋታ በሰራው ጥፋት ቀይ ካርድ መመልከቱ ይታወሳል።
በዚሁ ቅጣት ምክንያት ሀገሩ ከአርሜንያ ያደረገችው የምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ እንዳለፈውም ይታወሳል።
የ40 ዓመቱ ተጫዋች በወቅቱ የሁለት ጨዋታ ቅጣት ይጠብቀዋል ቢባልም አንደኛው ቅጣት ተነስቶለታል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቀጣይ ክረምት በሚካሄደው የዓለም ዋንጫ በመጀመርያው ጨዋታ መሰለፍ እንደሚችል ይፋ ሆናኗል።
የአምስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ አስተናጋጅነት በሚካሄደው ዓለም ዋንጫ ለ6ኛ ጊዜ የሚሳተፍ ይሆናል።
በአንተነህ ሲሳይ