Search

ማንችስተር ሲቲ በኒውካስትል ተሸነፈ

ቅዳሜ ኅዳር 13, 2018 82

በ12ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንችስተር ሲቲ በኒውካስትል ዩናይትድ 2 ለ 1 ተሸንፏል፡፡
በሴንትጄምስ ፓርክ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሃርቪ ባርንስ የኒውካስትል ዩናይትድን ሁለት ግቦች አስቆጥሯል፡፡
ሃርቪ ባርንስ ከ23 ዓመት በኋላ ማንችስተር ሲቲ ላይ ሁለት ግብ ያስቆጠረ የመጀመርያው የኒውካስትል ተጫዋች ሆኗል፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ በአንድ ጨዋታ ሲቲ ላይ ሁለት ግብ ያስቆጠረው ተጫዋች አለን ሽረር እንደነበር ይታወሳል፡፡
ሦስቱም ግቦች በስድስት ደቂቃ ልዩነት በተቆጠሩበት ጨዋታ ሩብን ዲያዝ የሲቲን አንድ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ የሚያጠብበትን አጋጣሚ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
የሊጉ መሪ አርሰናል ነገ በሰሜን ለንደን ደርቢ ከቶተንሀም ሆትስፐር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
 
በአንተነህ ሲሳይ