Search

ኤቤሬቺ ኤዜ ሀትሪክ በሰራበት ጨዋታ አርሰናል ቶተንሀምን አሸነፈ

እሑድ ኅዳር 14, 2018 165

በ12ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ በሰሜን ለንደን ደርቢ አርሰናል ቶተንሀም ሆትስፐርን 4 ለ 1 አሸንፏል፡፡

በኤምሬትስ በተደረገው ጨዋታ ኤቤሬቺ ኤዜ ሦስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርቷል፡፡ ሌአንድሮ ትሮሳርድ ደግሞ አንድ ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች ነው፡፡

ከጨዋታው አንድ ቀን በፊት በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ኤዜ ማነው በማለት ሊቀልዱ የሞከሩት የቶተንሀሙ አሰልጣኝ ቶማስ ፍራንክ እንግሊዛዊው ተጫዋች ሀትሪክ በመስራት በሚገባ መልስ ሰጥቷቸዋል፡፡

በጨዋታው ሪቻርልሰን የቶተንሀምን ብቸኛ ግብ አስገኝቷል፡፡

212ኛውን የሰሜን ለንደን ደርቢ በድል ያጠናቀቁት መድፈኞቹ ከተከታያቸው ቼልሲ ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት በማስፋት ሊጉን በ29 ነጥብ እየመሩ ይገኛሉ፡፡

በአንተነህ ሲሳይ