ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን ለጎን ከተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፤ ከቡድን 20 ጉባኤ ጎን ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ውይይቱ የባለብዙ ወገን ግንኙነትን ለማጠናከር ብሎም እንደ የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራ፣ ሰላም እና ፀጥታ፣ ዘላቂ ልማት ያሉ የጋራ አለምአቀፋዊ ትኩረት በሚጠናከርበት መንገድ ላይ ያጠነጠነ እንደነበር ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የCOP32 አስተናጋጅ ሀገር እንደመሆኗ መጠን ሊደረግ ስለሚችለው ድጋፍም ዙሪያ መወያየታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል።
#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #PMAbiy #PMOEthiopia #G20Summit