በ1.5 ቢሊየን ብር ወጪ እየተገነባ ያለው የነጌሌ ቦረና አየር ማረፊያ 89 በመቶ በመጠናቀቁ ከሁለት ወራት በኋላ ሥራ እንደሚጀምር በኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ቦረና ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱረዛቅ ሁሴን ገለጹ።
የአየር ማረፊያው ግንባታ የኅብረተሰቡ የረጅም ጊዜ የልማት ጥያቄ እንደነበር ያስታወሱት አቶ አብዱረዛቅ፣ መንግሥት ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የጀመረው ግዙፍ ግንባታ የማጠናቀቂያው ምዕራፍ ላይ መድረሱን አመላክተዋል።

የአየር ማረፊያው ወደሥራ መግባት የአካባቢውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ይበልጥ እንደሚያሳድገውም ይጠበቃል ብለዋል።
ባለፉት ጥቂት ዓመታት የኅብረተሰቡን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችሉ መሰል ትላልቅ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑም ተጠቁሟል።
በጀማል ነጌሶ