Search

ኢትዮጵያ ተዘንግተው አቧራ የለበሱ የቱሪዝም ሀብቶቿን ወደ አሻራ በመቀየር ጥቅም ላይ ማዋል ችላለች

ቅዳሜ ኅዳር 20, 2018 190

ኢትዮጵያ ተዘንግተው አቧራ የለበሱ የቱሪዝም ሀብቶቿን ወደ አሻራ በመቀየር ጥቅም ላይ ማዋል ችላለች ሲል የፌዴራል የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ገለጸ።

የፌዴራል የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ገዛኸኝ አባተ ከኢቲቪ ዜና ኢትዮጵያ መሰናዶ ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ ኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫ በቱሪዝም ሀብት የታደለች ሀገር ስለመሆኗ አንስተዋል።

ብዙ ሀገራት ተደምረው የሌላቸውን የተፈጥሮ ሀብት ኢትዮጵያ ብቻዋን የያዘች በመሆኗ ብዙዎች ኢትዮጵያ የታደለች ሀገር  ስለመሆኗ ያነሳሉ ሲሉ ገልጸዋል።

ይሁንና ታይተው የማይጠገቡ በርካታ የቱሪዝም ሀብቶቿ ለረጅም ጊዜ ተዘንግተው አቧራ ለብሰው ቆይተው እንደነበር ጠቅሰዋል።

ይህን አበክሮ የተገነዘበው የመደመር መንግሥትም፥እነዚን ሀብቶች ለምን አልምቶ መጠቀም አልተቻለም?” በማለት አቧራቸውን ማራገፍ የጀመረው ገና ከለውጡ ማግሥት በ“ገበታ” ፕሮጀክቶች መሆኑን አንስተዋል።

የለውጡ መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረትገበታ  ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር እና በገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች በርካታ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን መገንባት መቻሉንም ነው የተናገሩት።

መዳረሻዎቹ  የየአካባቢውን የተደበቀ ውበት በመግለጥ ገፅታቸውን  የለወጡ፣ ሀብቶቻቸውን ወደ ተጨባጭ ጥቅም የቀየሩ፣ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድልም የፈጠሩ እንደሆኑ ገልጸዋል።

የመሠረተ ልማት እጥረት እና እርጅና ተጭኗቸው የቆዩ ነባር መዳረሻዎችንም መልሶ በማልማት ለነዋሪዎች እና ለጎብኚዎች ምቹ እንዲሆኑ ስለመደረጉም አክለዋል።

ቱሪስቶችን ለማስጎብኘት ይቸገሩ ለነበሩ አስጎብኚዎች አሁን ላይ አማራጩ ስለመስፋቱ እና ዘርፉ ለሀገራዊ ኢኮኖሚው የሚያበረክተው ድርሻም እያደገ ስለመምጣቱ አቶ ገዛኸኝ አብራርተዋል

በሜሮን ንብረት

#ebcdotstream #ethiopia #tourism #attractions #ገበታለሀገር #ገበታለሸገር #ገበታለትውልድ